Posts

ነፍጠኝነትን የግል ርስት አድርጎ የነፍጠኛ ሥርዓት ባላደራና ጠባቂ መሆን: ከነፍጠኝነት የባሰ አሳፋሪ አረመኔያዊ (savage) ተግባር ነው!

Image
  ነፍጠኝነትን የግል ርስት አድርጎ የነፍጠኛ ሥርዓት ባላደራና ጠባቂ  መሆን፣ ከነፍጠኝነት የባሰ አሳፋሪ  አረመኔያዊ (savage) ተግባር ነው! በ Dr. Tsegaye Ararssa 📌📌📌📌📌 ነፍጠኛና ነፍጠኝነት ሲወቀስ አንተን ብቻ በተለይ የሚቆጠቁጥህ ከሆነ: ወይ እራስህ "ዘመናዊ" ነፍጠኛ ነህ: ወይ የነፍጠኛ(-ገባር) ሥርዓትን መልሰህ ለማቆም የምትተጋ  ቀልባሽ (reactionary) የፖለቲካ ኃይል ነህ::  ትምክህተኛ ሲኮነን አንተን ብቻ በተለየ ሁኔታ የሚያንገበግብህ  ከሆነም: በተመሳሳይ መልኩ : ወይ የአንድ ቡድንን የበላይነት የምታቀነቅን ትምክህተኛ (chauvinist) ነህ: ወይም በትምክህት ላይ የተመሠረተ ሥርዓትና አገረ-መንግሥት ለማቆም የምትተጋ የሕዝቦች እኩልነትና ወንድማማችነት ጠላት ነህ::  እነነውር ጌጡ: ነፍጠኛነትን ለፍትህ ከሚታገሉ ተራማጅ ኃይሎች ሁሉ ጋር በአንድነት ሁነው በመኮነን አሰላለፋቸውን ከዘመኑ ጋር ከማስተካከል ይልቅ: የነፍጠኛነት ጠበቃ ሆነው: አለፍ ሲልም "ነፍጠኛ ነኝ" የሚል ጽሑፍ የተከተበበት ልብስ ለብሰው በትውልዱ ላይ ይፎክራሉ:: ይሄም ሳያንስ: "ለምን ቃሉን ታነሳሳላችሁ? ቃሉን መጠቀምም የጥላቻ ንግግር ነው" ሊሉ ይቃጣቸዋል::   ሥርዓቱ: ተግባሩና በሕዝቦች ላይ ያደረሰው መጥነ-ሰፊ ጥፋት ሳያስቆጣቸው: ቃሉን አንስተን ሥርዓቱንና ተግባሩን መኮነናችን ያስቆጣቸዋል:: ክፋትን አትኮንኑ ወይም አወድሱልን ሊሉን ይፈልጋሉ::  ክፋትን አለመኮነን: ክፉ ተግባሩንና ውጤቱን እንደ በጎነት ተቀብሎ ማጽደቅ ነው:: ከክፋት ተግባሩ ፈፃሚዎች ጋር መተባበር ነው:: ይሄ ደግሞ ግፍ ከመፈጸም አልፎ የግፍ ተጠቂዎችን ፍትህ መቅበር ነው:: ሁለት በደል ነ...

Yooyyaa

Yooyyaa! Jirra jirtuu. Kuni biloogii Ibsaa Gammadaati. Karaa kanaanis dhufuuf jirraati, quba qabaadhaa.