ነፍጠኝነትን የግል ርስት አድርጎ የነፍጠኛ ሥርዓት ባላደራና ጠባቂ መሆን: ከነፍጠኝነት የባሰ አሳፋሪ አረመኔያዊ (savage) ተግባር ነው!
ነፍጠኝነትን የግል ርስት አድርጎ የነፍጠኛ ሥርዓት ባላደራና ጠባቂ መሆን፣ ከነፍጠኝነት የባሰ አሳፋሪ አረመኔያዊ (savage) ተግባር ነው!
በ Dr. Tsegaye Ararssa
📌📌📌📌📌
ነፍጠኛና ነፍጠኝነት ሲወቀስ አንተን ብቻ በተለይ የሚቆጠቁጥህ ከሆነ: ወይ እራስህ "ዘመናዊ" ነፍጠኛ ነህ: ወይ የነፍጠኛ(-ገባር) ሥርዓትን መልሰህ ለማቆም የምትተጋ ቀልባሽ (reactionary) የፖለቲካ ኃይል ነህ::
ትምክህተኛ ሲኮነን አንተን ብቻ በተለየ ሁኔታ የሚያንገበግብህ ከሆነም: በተመሳሳይ መልኩ : ወይ የአንድ ቡድንን የበላይነት የምታቀነቅን ትምክህተኛ (chauvinist) ነህ: ወይም በትምክህት ላይ የተመሠረተ ሥርዓትና አገረ-መንግሥት ለማቆም የምትተጋ የሕዝቦች እኩልነትና ወንድማማችነት ጠላት ነህ::
እነነውር ጌጡ: ነፍጠኛነትን ለፍትህ ከሚታገሉ ተራማጅ ኃይሎች ሁሉ ጋር በአንድነት ሁነው በመኮነን አሰላለፋቸውን ከዘመኑ ጋር ከማስተካከል ይልቅ: የነፍጠኛነት ጠበቃ ሆነው: አለፍ ሲልም "ነፍጠኛ ነኝ" የሚል ጽሑፍ የተከተበበት ልብስ ለብሰው በትውልዱ ላይ ይፎክራሉ::
ይሄም ሳያንስ: "ለምን ቃሉን ታነሳሳላችሁ? ቃሉን መጠቀምም የጥላቻ ንግግር ነው" ሊሉ ይቃጣቸዋል::
ሥርዓቱ: ተግባሩና በሕዝቦች ላይ ያደረሰው መጥነ-ሰፊ ጥፋት ሳያስቆጣቸው: ቃሉን አንስተን ሥርዓቱንና ተግባሩን መኮነናችን ያስቆጣቸዋል::
ክፋትን አትኮንኑ ወይም አወድሱልን ሊሉን ይፈልጋሉ::
ክፋትን አለመኮነን: ክፉ ተግባሩንና ውጤቱን እንደ በጎነት ተቀብሎ ማጽደቅ ነው:: ከክፋት ተግባሩ ፈፃሚዎች ጋር መተባበር ነው:: ይሄ ደግሞ ግፍ ከመፈጸም አልፎ የግፍ ተጠቂዎችን ፍትህ መቅበር ነው:: ሁለት በደል ነው:: አንድእኛ: በህዝብ ላይ ግፍና ኢፍትሃዊነትን መፈጸም ነው:: ሁለተኛ: የግፍ ታሪክንና ሃቅን: እንዲሁም የተጠቂዎችን የተኖረ መከራ (ትውስታቸውንና ትዝታቸውን) መቅበር ማዳፈን ወይም መሰረዝ ነው:: አረመኔነት (savagery) ነው::
ከሁሉም በላይ ደግሞ: ዛሬ: በዚህ ባሁኑ ዘመን: ያንኑ ግፍ ለመድግም በትውልዱ ላይ መዛትና ለማስፈራራት መሞከር ነው:: የጥላቻና የሽብር ንግግርን መንዛት ነው:: ለግፈኞች ተቆርቁሮ: ተጠቂዎችን (ወይም ትሩፋኑን) እውነታቸውን እንዳይናገሩ ማሸማቀቅ ነው:: አሸማቃቂዎቹም የነፍጠኛው ሥርዓት ወራሽ: ባላደራና: አራማጅ (undertaker) መሆናቸውን በይፋ ማረጋገጥ ነው::
አንተን የነፍጠኝነትና የትምክህተኝነት ጠበቃ መሆንህ ሳያሳፍርህ: እኔ የነፍጠኝነትን ክፋት: ያስከተለውንና ዛሬም እያስከተለ ያለውን የግፍ ክምር መውቀሴ በምን ሂሳብ:ለምንና እንዴት ያሳፍረኛል: ያስወቅሰኛል?
ግፍ ባትፈሩ: ነውርን መፍራት ነበረባችሁ:: በነውር ማጌጣችሁ ሳያንስ: የነውራችሁን ነውርነት መግለፅ የጥላቻ ንግግር ነው ስትሉ: ጥላቻችሁ ምንኛ እንዳሳወራችሁ አጋለጣችሁ::
አዎን: ደግሜ እላለሁ:: ነፍጠኝነት ወንጀል ነው:: ወሮ-በላነት ነው:: ነፍጠኝነት ጦረኝነት ነው:: ወራሪ-ነጣቂነት ነው:: እንደ lynching ያለ የጥላቻ ፍጅት ተግባር ነው:: በታሪክም ቢሆን: የነፍጠኛ-ገባር ሥርዓት: ዓላማውም ውጤቱም: ዘራፊ-ቀማኛነት: አሸባሪ-ገዳይነት: ዘር-አጥፊ ወንጀለኝነት ነው::
("ነፍጠኝነትን የኛ (የብቻችን ርስት) ነው: ነፍጠኞች እኛ ነን: ነፍጠኛን መጥላት እኛን መጥላት ነው: ነፍጠኛን መኮነን እኛን መኮነን ነው" ለሚሉ: ነውርን እንደጌጥ ለሚሻሙና ነውራችንን አወድሱ-መርቁልን ለሚሉ ተላላዎች የተፃፈ::)
📌📌📌📌📌
.jpg)
Comments
Post a Comment